ትንሽ ፡ ስለእኛ፡ እንግለፅልዎት።

የዙሪክ፡ባኖሆፍ(ባቡር፡ጣቢያ)፡መድኃኒት፡ቤት፡በሲዊዝ፡ውስጥ፡ትልቁና፡ተወዳጁ፡መድሃኒት፡ቤት፡ነው።

የሚገኘውም፡በቀላሉ፡ሊደረስበት፡በሚችለው፡እና፡ታሪካዊ፡በሆነው፡በዋናው፡የዙሪክ፡ባቡር፡ጣቢያ፡በዙሪክ፡ከተማ፡ዉስጥ፡ነው። በየቀኑ፡አመቱን፡በሙሉእሁድና፡በአል፡ቀንም፡ጨምሮ፡ከጠዋቱ፡አንድ፡ሰዓት፡እስከ፡ለሊቱ፡ ስድስት፡ ሰዓት፡ ክፍት ፡ ሆኖ፡ ይጠብቃል።

እርስዎ:በዙሪክ:ከተማ:ንዋሪ:ወይም:አቋርጠው:የሚያልፉ:ቤሆኑ:መድሃኒት:ቤታችን:ስለጤናዎ:ወይም:ስለ:ውበትዎ:ጥያቄ:ካለዎት:የመጀመሪያ:ተመራጭ:ነው።

ከመቶ:የሚበልጡ:የመድሃኒት:ቤታችን:ሠራተኞች:በፋርማሲ:ሙያ:የሰለጠኑ:ፋርማሲስቶች:የፋርማሲ:እርዳቶችና:ድሮጊስቶች:በተለያዩ:20ልዩ:ልዩ:ቋንቋዎች:ስለ:ጤናዎት:ምከር:ለመስጠት:እና:በመድኃኒት:ቤታችን:ውስጥ:በሚገኙት:ከ17,000 በሚበልጡ:የመድሃኒትየጤና:እና:የመዋቢያ:ምርቶች:የትኛው:ለእርሶዎ:ተስማሚ:እንደሆነ:ሊያስረድዎት:ተዘጋጅተው:ይጠብቃሉ።

ምክር:በጤና:ባለሙያ

መድኒኃት:ቤታችን:ከመላው:አገሩቱ:በፋርማሲ:እውቀታቸው:የበለፀጉና:የሥራ:ፍላጐት:ባላቸው:ባለሙያዎች:የተሞላ:ነው።እንዲሁም:ቀጣይና ተከታታይ:

የሙያ:ስልጠና:እና:የቅርብ:ክትትል:እያደረግን:ለደንበኞቻችን:የተሟላ:እና:ብቃት ያለው:ምክር:እንሰጣለን:: ዋናው:አላማችን:ሰራተኞቻችን:በሥራ:ቦታቸው፡ላይ፡ጥሩ፡የሥራ፡ስሜት፡እንዲያድርባቸዉ፡እና ፡ ሙያቸውን፡ በፍቅር ፡ እንዲወጡ፡ እያበረታታን፡ ለእርስዎም፡እንዲሁ፡ያለዎትን፡ችግር፡በግልፅ ማስረዳት፡እንዲችሉ፡ቦታና፡ጊዜ፡እንሰጣለን።ሐኪም፡ከአስፈለገዎትም፡ከእኛ፡ብዙም፡ሳይርቁ፡ከሚገኙ፡የሕክምና፡ባለሞያዎችና፡እስፔሻሊሥቶች፡ጋር፡እናገናኛለን።

የመድሃኒት:ማዘዥ:

መድሃኒት:ቤታችን:በመጀመሪያ:ደረጃ:በሐኪም:ወይም:ከሆሲፒታል:ለሚታዘዙ:መድሃኒቶች:እንደአስፈላጊነቱ:ማቅረብ:እንችላለን።በግምጃ:ቤታችን:የማ
ይገኝም:ቢሆን:በቀን:5ጊዜ:ከዋናው:የመድሃኒት:ግምጃ:ቤት:ስለሚደርሰን:ያስፈለገዎት:መድሃኒት:በተወሰነ:ስዓት:ውስጥ:እናቀርባለን።

የቅመማ:ክፍላችን (ላባራቶር)

መድሃኒት:ቤታችን:የተሟላ:የራሱ:የሆነ:ዘመናዊ:የሆነ:ላባራቶርና:በሙያው:የሰለጠኑ:ባለሙያዎች ፡ ያሉት፡ ተቋም፡ እንደመሆኑ፡ መጠን፡ ከባለ ሙያ፡ የሚታዘዝልዎ፡ የተለየ፡የቅመማ: ትዕዛዝ፡ ቢኖር ፡ ጥራቱ፡ በተረጋገጠና፡በአስተማማኝ፡ መንገድ፡ አዘጋጅተን፡ እናቀርብልዎታለን።

ያለ:ሐኪም:ማዘዥ:የሚሰጡ:መድሃኒቶች:

ያለ:ሐኪም:ትእዛዝ:የሚሰጡ:መድሃኒቶች:በብዛት:ይገኛሉ ፡ባለሙያዎቻችን:ለእርስዎ:የሚስማማውን:እማይጎዳዎትን:እና:በትክክል:ሊጠቀሙበት:የሚችሉትን:በማማከር:ይሰጡዎታል።

ተጨማሪ:ባሕላዊ:የሆኑ:መድሃኒቶች (ኮምፕለሜንቴር፡ ሜዲሲን)

በባሕላዊ:መድሃኒት:የሰለጠኑ:ሙያተኞቻችን:የትኛው:የባሕል:መድሃኒት:የበለጠ:እንደሚረዳዎት:ለምሳሌ ፡ሆሞፓቲ፣ ፎቶቲራፒ  ከእፅዎት የሚገኝ፡ መድኋኔት ፣ እስፓግሪክ፣ ሽሉስልሳልዝ፣ባክብሉትን፣ ቬታልእስቶፍ፣ ኦርቶሞሎኪላር ሚድስን እና ተጨማሪ፡ ምግቦች ፡ ለምሳሌ ፡ቯይታሚን፡ ሚነራልእስቱፍ ፣ ወዘተ ምክር:ይሰጣሉ።

ተጨማሪ:የሙያተኛ:ምክርና፡ አገልግሎቶች

የወሊድ:መቆጣጠሪያ:ኪኒን:አጠቃቀም፣የቁስል:ሕክምና፣የቤት፣የአደጋ:እና:የጉዞ:ጊዜ:ሕመም:መከላኪያ:መድሃኒቶች:እራስን:በራስ:ማከም:እንዲችሉ:ምክር:ይሰጣሉ።

       እረዥም:ጊዜ:የሕክምና:ክትትል:የሚያስፈልገው:በሽታ:ካለብዎት:አስፈላጊውን:የሕክምና:ምክር:እንሰጣለን።ለምሳሌ:የስኳር:የአስም:በሽታና፡ የመሳሰሉ፡ ሕመም፡ ካለብዎ፡ ባለሙያዎቻችን ፡ የመድኃኒቶቹንና፡ የመሣርያዎቹን ፡ አጠቃቀም፡ ያስረዳሉ።

የሽቶ:ክፍላችን

የውበት:አጠቃቀም:ምክር

በውበት:እንክብካቤ:አጠቃቀም:ምክር:የሰለጠኑ:ሙያተኞቻችን:ባለን:የውበት:መጠቀሚያ:ምርቶቻችን:ስም:ላይ:ጥገኛ:ሳይሆኑ:ለእርስዎ:ቆዳ:
ተስማሚ:የሆነውን:መርጠው:ያቀርብሎዎታል። ለምሳሌ፡ ቡግር፣ ደረቅ፡ ቆዳ ፡ ወይም የተለየ ጥቃንቄ፡ የሚያስፈልገው ፡የቆዳ ፡ ዓይነት፡ ከለዎት፡ ባለሙያዎቻችን፡ ምክርና፡ ተስማሚውን ፡ የቅባት ፡ ዓይነት፡ ይሰጣሉ።

ሽቶና:መዋቢያ

በቅርብ፡ የወጡ ፡  የውበት ፡ መገልያዎችና ፡ አዳዲስ ፡ ሽቶውችን፡በመድሃኒት:ቤታችን:የሽቶ:ክፍል:ውስጥ:ስለሚገኙ:በአስፈላጉዎት:ጊዜ:መጥተው:በማየትና:በመሞከር: እራስዎትን:አስደስተው:መግዛት:ይችላሉ።

በራስዎት:ምርጫ:መግዛት:በሚችሉት:ክፍላችን:ውስጥ:የሚገኙ:ምርቶች

፦የልጆች:ምግብና:ጡጦ:እንዲሁም:የልጆችን:ንፅሕና:መጠበቅ:የሚችሉበት
ምርቶች:               
፦ ለእስፖርተኞች:የሚያስፈልጉ:ምግቦች።
፦ ለእግር:እንከብካቤ:የሚያስፈልጉ:ቅባቶች:
፦ የፀጉር:ቀለምና:እንከብካቤ:ምርቶች:
፦ ዲዎዱራትና:የፂም:መላጮች:ምርቶች:
፦ የፀሐይ:መከላከያ:ምርቶች:
፦ የጥርስ:እንከብከቤ:ምርቶች:
፦ ሊንዘን:ማፅጃ:የኮንታክት:ሌንዝ:ማፅጃ:ምርቶች
፦ የቁስል:ሕክምና:ምርቶች:ለምሳሌ:ፕላስተር:እና:የቁሰል:ማፅጃ:ምርቶች:
፦ ባንዴጅ:የተለያዩ
፦ ለሴቶች:ንፅሕና:አጠባበቅ:የሚያስፈልጉ:የተለያየ:ሞዴሶች:
፦ የተለያዬ:ማርክ:ያላቸው:ኮንዶሞች:
፦ የተፈጥሮ:የሆኑ:ጭማቄዎች:የተለያዩ:የሻይ:አይነቶች:
፦የተለያዩ:የነፍሳት:መከላከያ:እና:ልዩ:ልዩ:የልብስና:የቤት:ማፅጃ:ምርቶችና፣ ወዘተ..            

የፁሁፉ ትርጉም፣ በትዝታ፡ተፈራ